Wednesday, October 16, 2024
spot_img

ወደ ካርቱም ተጠርተው የነበሩት በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 10፣ 2013 ― ከሁለት ሳምንት በፊት በአገራቸው ሱዳን የተጠሩት በአዲስ አበባ ይገኙ የነበሩት የአገሪቱ አምባሳደር ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ተነግሯል፡፡

ወደ ካርቱም ተጠርተው የነበሩት በአዲስ አበባ የሱዳን አምባሳደር ከዛሬ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብደላ ሃምዶክ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ በወቅቱ ወደ ካርቱም የተጠሩት ሱዳን የፌደራል መንግስቱን እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ህወሓት ጋር ላደራድር በሚል ላቀረበችው ጥያቄ ኢትዮጵያ ፈቃደኛ አለመሆኗን ተከትሎ ከመንግስታቸው ጋር ለመመካከር ነበር።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት አገራቸው አሁንም ኢትዮጵያን መርዳት ትፈልጋለች መለታቸውን አል ዐይን ዘግቧል፡፡

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ችግር ላይ በነበርንበት የሽግግር ጊዜ እኛን መጥቶ ለመርዳት ፈቃዳችን አላስፈለገውም ነበር፤ እና እኛም ብድር የመመለሻችን ጊዜ አሁን ነው ብለን እናስባለን፤ ምክንያቱም አንድነቷ እና ደህንነቷ የተጠበቀ፣የተረጋጋች ኢትዮጵያን ማየት ለእኛ ትልቅ ነገር ነው፡፡

በምንመራው ቀጣናዊ ተቋም ኢጋድ በኩል ይህን የማድረግ ኃላፊነት እንዳለብንም እናስባለን›› ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሊቀመንበር የሆነችው ሱዳን፣ የኢትዮጵያን መንግስት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ህወሓት ጋር ለማደራደር ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ከሩዋንዳው ፖል ካጋሜ፣ ከደቡብ አፍሪካው ሲሪል ራማፎዛ እና ከአሜሪካ ጋር በመወያየት ላይ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img