Wednesday, October 16, 2024
spot_img

ኮቪድ-19 በድጋሚ እያገረሸ ነው ሲሉ ጤና ሚኒስትሯ አሳሰቡ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 8፣ 2013 ― የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ “ኮቪድ-19 በድጋሚ እያገረሸ ነው” ሲሉ አሳሰቡ፡፡

ሚኒስትሯ የጽኑ ህሙማን ቁጥርም እየጨመረ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የፊትና የአፍ መሸፈኛ ጭምብል እንዲደረግ፣ መሰባሰቦች እንዲቀንሱ፣ ንጽህና እና አካላዊ ርቀት እንዲጠበቅ፣ ክትባት እንዲወሰድም ነው ሚኒስትሯ ያሳሰቡት፡፡

ከሰሞኑ የጤና ሚኒስቴር ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በተለየ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋባት በመዲናዋ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር እድሜያቸዉ ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች እንደሚሰጥ ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺ 430 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 975 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 288 ሺ 159 ደርሷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img