Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአፍሪካ ኅብረት ባልደረባ የሆኑ አንድ ኢትዮጵያዊ ሳማንታ ፓወርን የሚያብጠለጠል የትዊተር መልእክት በኅብረቱ ኦፌላዊ የትዊተር አካውንት ተጠቅመው ማስተላለፋቸው ውዝግብ ፈጠረ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 8፣ 2013 ― የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃኪ ሱሊቫን በትግራይ ጦርነት ተፋላሚዎች ‹‹ወደ ድርድር ጠረጴዛ በአስቸኳይ እንዲመጡ›› ማለታቸውን ተከትሎ ሐሳቡን የደገፉት የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር፣ ይህንኑ በማጠናከር ‹‹ለዚህ ግጭት ወታደራዊ መፍትሔ የለም፣ ሁሉም አካላት ለመነጋገር ካልተስማሙ ከዚህ የከፋ ችግር ይፈጠራል›› ሲሉ ለጻፉት የትዊተር መልዕክት የአፍሪካ ኅብረት ባልደረባ የሆኑ አንድ ኢትዮጵያዊ ኃላፊዋን የሚያብጠለጠል ምላሽ በኅብረቱ ኦፌላዊ የትዊተር አካውንት ተጠቅመው ማስተላለፋቸው ውዝግብ ፈጥሯል።

ከምልልሱ ጥቂት ቆይታ በኋላ ምላሹን ማንሳቱን ያስታወቀው የአፍሪካ ኅብረት፣ በዚያው አካውንት ባልደረባው የኅብረቱን የሥነ ምግባር ደንቦች ጥሶ የግል አቋሙን ማንጸባረቁን የገለጸ ሲሆን፣ የተሰጠው ምላሽም የባልደረባው እንደሆነና ጉዳዩን በውስጥ እንደሚመረምር አስታውቋል፡፡

ኅብረቱ በዚህ ማስታወሻው የምላሽ ሰጪውን ማንነት ባይጠቅስም፣ ድርጊቱ የተፈጸመው ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው የኅብረቱ ባልደረባ መሆኑን የኅብረቱ ሹም አረጋግጠውልኛል ሲል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜግነት ባላቸው የአፍሪካ ኅብረት ባልደረባ አስተያየታቸው የተብጠለጠለባቸው የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ከቀናት በፊት ኢትዮጵያ ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ መመለሳቸው ይታወሳል።

ሳማንታ ፓወር በቅርብ ጊዜያት በኢትዮጵያ ጉዳይ በሚሰጧቸው ተደጋጋሚ አስተያየቶች በኢትዮጵያውያን ዘንድ በሰፊው የሚታወቁ ሆነዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img