Friday, November 22, 2024
spot_img

ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ከሁለት ዓመት በፊት በወታደራዊ መስክ ለመተባበር ያደረገችውን ስምምነት አገደች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― የፈረንሳይ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ከሁለት ዓመት በፊት በወታደራዊ መስክ ትብብር ለማድረግ የፈፀመውን ስምምነት ማገዱን የአገሪቱ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።

አገሪቱ የውል ስምምነቱን ያገደችው በትግራይ ባለው ሁኔታ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሁለት ባለሥልጣናት መስማቱን የዜና ወኪሉ አመልክቷል።

ታግዷል የተባለው የሁለቱ አገራት ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሁለት ዓመብ በፊት ያደረጉት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በስምምነቱ መሠረት ፈረንሳይ ኢትዮጵያ ለምታቅደው የባሕር ኃይል ግንባታ የሚውል 85 ሚሊዮን ዩሮ ትሠጥ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img