Tuesday, October 15, 2024
spot_img

ደቡብ ኮሪያ ዜጎቿ ወደ አማራ ክልል ሁለት አካባቢዎች የሚያደርጓቸውን ጉዞዎች እንዲሠርዙ አሳሰበች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― ደቡብ ኮሪያ ወደ አማራ ክልል ጉዞ ለማድረግ እቅድ ያላቸው ዜጎቿ ጉዟቸውን እንዲሰርዙት አልያም እንዲያዘገዩት አሳስባለች፡፡

የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገሪቱን ዜጎች ያሳሰበው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ እና ምሥራቅ ጎጃም ለሚያደርጓቸው ጉዞዎች ነው፡፡

አገሪቱ ዜጎችዋ ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች ተጉዘው ከሆነም ደኅንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎች ላይ እንዲቆዩ ነው ያሳሰበችው፡፡

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በንቃት እየተከታተለ እንደሚገኝ የገለጸው የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ እንደ ሁኔታው ማስተካከያችን እንደሚያወጣም ጠቁሟል፡፡

የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጠቀሰው በተለይ በሰሜን ወሎ አካባቢ ጦርነት መኖሩን የሚያመለክቱ መረጃዎች በተደጋጋሚ ሲወጡ መሰንበታቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img