Tuesday, October 15, 2024
spot_img

ሰበር ዜና ባንኮች ንብረት በመያዣነት ተጠቅመው ብድር እንዳይሰጡ ታገዱ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 6፣ 2013 ― በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች መሬት፣ ቤት፣ ህንፃ ሆነ ሌሎች ነገሮችን በመያዣነት ተጠቅመው ለጊዜው ምንም አይነት ብድር እንዳይሰጡ ታግደዋል።

መመሪያውን ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስትር ናቸው። ትእዛዙ ከብሔራዊ ባንክ ለባንኮቹ ፕሬዚዳንቶች የተላለፈው በአጭር የፅሁፍ መልእክት (SMS) መሆኑም ታውቋል።

በዚሁ መሠረት ባንኮች ለጊዜው ማንኛውንም ህንፃ፣ ቤት ፣ መሬት በመያዣነት ተጠቅመው ብድር እንዳለቁ አሳስበዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ሆን ተብሎ እየተሰራ መሆኑ አንስተው የገበያውን መናጋት ለማስተካከል ቶሎ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት በመግለፅ ጉዳዩ አደጋው ብዙ በመሆኑ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ሲሉ መናገራቸውን ሸገር ዘግቧል።

ዶክተር ኢዮብ አክለውም የፀጥታ ተቋም የብሄራዊ ባንክ የተናበበ ስራ መስራት መጀመራቸውን አስረድተዋል ነው የተባለው።

“የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ ይልካል ፤ የቤት ብድር ምናምን እያሉ የሚወሰዱ ገንዘቦች ለጥቁር ገበያው እንደሚውሉ ስለሚታወቅ ባንኮች በእንደዚህ ያሉ ነገሮች ላይ ንቁ ሆነው እንዲሰሩ መመሪያ እየተላከላቸው ነው ፤ ሰውም ባንኮችም ንቁ መሆን አለባቸው” ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር አያሌው በበኩላቸው ሌላ አዲስ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ ባንኮች መሬት፣ ህንፃ ቤት ሌሎች ነገሮች አስይዘው ማበደር እንደማይችሉ መግለፃቸውም ተዘግቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img