Monday, September 23, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ‘ዴልታ’ የተሰኘውን አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ እስከሁን ለመመርመር አልቻለችም ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 6፣ 2013 ― በኢትዮጵያ ‘ዴልታ’ የተሰኘውን ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መመርመር አለመጀመሩን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ እስካሁን ‘ዴልታ’ የተሰኘውን አዲስ ልውጥ የኮቪድ ዝርያ መመርመር አልጀመረችም።

እንደ ዶ/ር ሊያ ገለጻ ምርመራው እስካሁን ያልተጀመረው ዝርያውን ለመመርመር የሚያስፈልገው ኬሚካል ወይም ‘ሪኤጀንት እስካሁን ወደ አገር ውስጥ ባለመኖሩ ነው፡፡

ዶ/ር ሊያ ይሁንና ‹‹ኬሚካሉን ከውጭ አገር ለማስገባት በሂደት ላይ በመሆናችን በቅርቡ ምርመራው ይጀመራል›› ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የአፍና የፊት መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር በአዲስ አበባ 59 በመቶ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ውጪ 20 በመቶ መሆኑም ተገልጧል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ሊያ ‹‹ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ ዜጎች፣በቫይረሱ የሚያዙ እና ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ›› በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥም ወደ ጽኑ ህክምና የሚገቡ ዜጎች በ2.5 በመቶ ሲያሻቅብ፣ በቫይረሱ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር ከ2.8 በመቶ ወደ 7.4 በመቶ ከፍ ሲል ህይወታቸው የሚያልፍ ዜጎች ቁጥር ደግም ከ13 በመቶ ወደ 36 በመቶ ማሻቀቡ በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img