Wednesday, November 27, 2024
spot_img

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ተሳትፎ በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት እንደሚጠበቁ አሳወቁ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 6፣ 2013 ― የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ተሳትፎ ዛሬ ማለዳ ወደ አገር ቤት የተመለሱ አትሌቶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት ሰደዋል፡፡

ፕሬዝዳንትዋ ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ ዘርፍ በተለይም በረዥም ርቀት ሩጫ ተሰልፈው ወርቅን ጨምሮ ሜዳሊያ ላስገኙና በአጠቃላይ ለተወዳደሩት አትሌቶች በሙሉ ምሥጋናቸውን ማቅረባቸውን ጽሕፈት ቤታቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

አትሌቶቹን ወደ ኦሎምፒክ ሲያቀኑ መሸኘታቸውን ያስታወሱት ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ፣ ሁኔታው እንዳመቸ ይፋዊ አቀባበል የሚዘጋጅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አክለውም በቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን ተሳትፎ በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት እንደሚጠበቁ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው የቶክዮ ኦሎምፒክ 1 የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሁለት የነሐስ በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎች አግኝታ ባለፉት 20 ዓመታት ከተገኘው ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግባለች፡፡

በውድድሩ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራሮች መካከል ቀድሞ ተከስቶ ወደ ቶክዮ የዘለቀው አለመግባባት በስፖርት ላይ ባተኮሩ የመገናኛ ብዙኃን ዝግጅቶች ጎልቶ ሲነገር ሰንብቷል፡፡

በቶኪዮ 2020 ኢትዮጵያ በ10 ሺሕ ሜትር በወንዶች በሰለሞን ባረጋ ወርቅ፣ በ3 ሺህ ሜትር በወንዶች መሠናክል በለሜቻ ግርማ ብር፣ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች በለተሰንበት ግደይ ነሐስ፣ በሴቶች 5ሺህ ሜትር በጉዳፍ ፀጋዬ ነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያ በማስመዝገብ በአለም 56ኛ፣ በአፍሪካ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img