Sunday, September 22, 2024
spot_img

መንግሥት የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን ሪፖርት አጣጣለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 6፣ 2013 ― የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትላንትናው እለት ያወጣውን በትግራይ ጦርንት ጦርነት ተፈጽመዋል የተባሉ መረጃዎች የያዘውን ሪፖርት አጣጥሎታል፡፡

መንግሥት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በኩል ባወጣው መረጃ፣ ተዓማኒነት የለውም ያለውን የአምነስቲ ሪፖርት የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ ላይ ጥያቄ አንስቷል፡፡

መንግሥት በመግለጫው የአምነስቲ መረጃ አሰባሰብ ዘዴ ተዓማኒነት የሌለው እንዲሁም ሱዳን በሚገኙ ስደተኛ መጠለያዎች እና ትግራይ ካሉ ሰዎች በርቀት በስልክ ብቻ በተደረጉ ቃለ ምልልሶች ላይ ብቻ የተመሠረተ ሪፖርት ነው ብሏል፡፡

አምነስቲ ኢንረትናሽናል ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግሥትን ስም ለማጥፋት ሐሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል ሲልም ከሷል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትግራይ ግጭት የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን በዳሰሰበት የጥናት ውጤት ከየካቲት እስከ ሚያዚያ ባለው ወቅት ብቻ ከ1 ሺሕ በላይ ሴቶች መደፈራቸውን ሪፖርት ማድረጋቸውን አመልክቷል፡፡

አምነስቲ ለሪፖርቱ ከኅዳር እስከ ሰኔ ወር ድረስ 63 ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ቃለ ምልልስ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን፣ እነዚህ የጥቃት ሰለባዎች 15ቱን በሱዳን በስደተኛ መጠለያዎች በአካል፣ 48 ሴቶችን ደግሞ በስልክ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑት የአምነስቲ ከፍተኛ መርማሪ ዶናቴላ ሮቬራ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲሁም የአማራ ኃይሎች በጥቃት አድራሽነት በተጠቂዎች መለየታቸውን ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img