Monday, October 14, 2024
spot_img

በአሸባሪነት የተፈርጁት ሕወሓት እና የኦነግ ሸኔ ቡድኖች የጦር ጥምረት ሰለመመስረታቸው ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 5፣ 2013 ― አሶሼትድ ፕረስ “የኦነግ ሸኔ” መሪ ጃል ማሮ ነገረኝ ብሎ እንደዘገበው በአሸባሪነት የተፈርጁት የኦነግ እና የህወሓት ቡድኖች የጦር ጥምረት መመስረታቸውን አስታውቀዋል።

የህወሓት ቡድን ስምምነቱ እንዲፈፀም ከሳምንታት በፊት ጥያቄ እንዳቀረበ እና እንደተቀበሉትም መሪው ተናግረዋል ሲል ዘገባው አስነብቧል።

ኩምሳ ድሪባ (ጃል ማሮ) ስምምነቱ የተመሰረተው የጋራ ጠላት ብለው በጠሩት የሀገሪቱ መከላከያ ሃይል ላይ ያነጣጠሩ የጦር ጉዳዮች ላይ መሆኑን መናገራቸውን አሶሼትድ ፕረስ አስፍሯል።

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ሌሎች ቡድኖችንም ለመቀላቀል እቅድ መኖሩን የቡድኑ መሪ መግለፃቸውም ተጠቅሷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img