Monday, September 23, 2024
spot_img

የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ኤርትራውያን ስደተኞችን እና የትግራይ ተፈናቃዮችን ለመርዳት 164.5 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 5፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ስደተኞችን ለመርዳት 164.5 ሚሊዮን ዶላር ጠይቋል።

የስደተኞች ኤጀንሲ ገንዘቡን የጠየቀው 96 ሺህ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ 650 ሺህ በትግራይ ክልል ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲሁም 120 ሺህ የሚሆኑ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመርዳት እንደሆነም ነው የገለጸው፡፡

የእርዳታው 61 በመቶ ማለትም 101.3 ሚልዮን ዶላሩ መጠለያ ጣብያዎች ለመገንባት፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶች ለማቅረብ እና በትግራይ ግጭት ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመርዳት የሚውል መሆኑንም ነው የገለጸው ኤጀንሲው፡፡

63.2 ሚልዮን ዶላሩ በሱዳን ለሚገኙ ስደተኞች የተለያዩ የመጠለያ፣ ውሃ፣ ጤና እና ሎጂስቲክስ አቅርቦቶች የሚውል እንደሆነም አክሏል።

ኤጀንሲው በሱዳን የሚገኙትን ስደተኞች በተመለከተ ባለፈው ወር ብቻ 40 ኤርትራውያንን ያካተቱ 275 ስደተኞች ወደ ሱዳኑ “ሃምዳይት መጠለያ ጣብያ” መግባታቸውን አስታውቋል፡፡

900 የሚሆኑ የቅማንት ተወላጆች ከአማራ ክልል በጋላባት በኩል ወደ ሱዳን መዝለቃቸውንና ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

ኤጀንሲው በመጨረሻም ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ኃይሎች የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ህጎች በማክበር የንጹሃንን ደህንነት እንዲጠብቁና ያልተገደበ እርዳታ እንቅስቃሴ እንዲኖር ኃላፊነታቸው እንዲወጡ ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img