አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 4፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር እንዳልተመለሰለት አስታውቋል፡፡
ከተሰጣቸው ብድር በውላቸው መሠረት ባለፉት ሁለት የክፍያ ጊዜያት 166 ቢሊዮን 518 ሚሊዮን 823 ከተሰጣቸው ብድር በውላቸው መሠረት ባለፉት ሁለት የክፍያ ጊዜያት 166 ቢሊዮን 518 ሚሊዮን 823 ሺሕ ብር የተመለሰ ሲሆን፣ በመክፍያ ጊዜው ያልመለሱ 11 ኅብረት ሥራ ማኅበራት 46 ቢሊዮን 203 ሚሊዮን 228 ሺሕ ብር እንዳልተመለሰለት ነው ያረጋገጠው፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ለግብርና እና ሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት የተፈቀደን 800 ሚሊዮን ብር ብድር ለ75 ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲሰራጭና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ክትትልና ድጋፍ መደረጉንም ተቋሙ አስታውቋል።
በ12 ክልሎች ለ86 ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ 877ሚሊዮን 496 ሺሕ 434 ብር ብድር ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ለ56 ኅብረት ስራ ማኅበራት ብር 366 ሚሊዮን 205 ሺሕ 768 በባንኩ ተፈቅዶ ከዚህ ውስጥ 45 ኅብረት ሥራ ማኅበራት ብር 345 ሚሊዮን 902 ሺሕ 132 መውሰድ መቻላቸው ተገልጿል።
ለ11 ኅብረት ሥራ ማኅበራት የተፈቀደውን 20 ሚሊዮን 303 ሺሕ 636 ብር ሁለቱ በወለድ አልባ፣ ሰባቱ በትግራይ ክልል ባለው የጸጥታ ምክንያት፣ ሁለት ደግሞ የግብር ከፋይ ምዝገባ ባለሟሟላታቸው ብድሩን መውሰድ አልቻሉም።
የብድር ጥያቄ ሰነድ ካቀረቡ 86 ኅብረት ሥራ ማኅበራት ውስጥ ለ30ዎቹ ብድሩ ያልተፈቀደላቸው ሲሆን፣ ለዚህም የተሰጠው ምክንያት 25 ማኅበራት 352 ሚሊዮን 250 ሺሕ ብር ከፍተኛ የብድር ዕዳ ያለባቸው መሆኑ፣ አንድ ማኅበር 2 ሚሊዮን ብር የግብይት አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ መሆን፣ እንዲሁም አራት ማኅበራት በ 38 ሚሊዮን ብር የኦዲት ሪፖርቶች ላይ ኪሳራ ላይ መሆናቸው ነው።
በዚህም ምክንያት እነዚህ ማኅበራት ብድር መውሰድ እንደማይችሉ ልማት ባንክ ማስታወቁን የዘገበው አዲስ ማለዳ ነው፡፡