Sunday, October 13, 2024
spot_img

ሕወሃትን የሚቃወም ሰልፍ በነገው እለት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 14፣ 2013 ― ሕወሃትን በመቃወም በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ እስከ አጋማሽ ቀን የሚካሄድ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አብዲ ፀጋዬን ዋቤ አድርጎ ብሔራዊ ቴሌቭዥን በማኅበራዊ ገጹ ዘግቧል።

ሰልፉ የሕዝብን ጥያቄ መሠረት በማደረግ የሚካሄድ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ የሰልፉ ዓላማ ሕወሃትን ከመቃወም ባለፈ ሕዝቡ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ደጀንነት ለመግለጽ ነው ብለዋል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ እና የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መከናወኑን ጨምሮ እስካሁን በሀገር ደረጃ የተገኙ ድሎች የሚወደሱበት መሆኑንም የጽ/ቤቱ ኃላፊ አክለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img