Monday, October 14, 2024
spot_img

አሜሪካ በኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት ለመሾም ፖለቲከኞችን እያሰባሰበች መሆኑን የብልጽግና ሹመኛው ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 14፣ 2013 ― አሜሪካ “የኢትዮጵያውያንን ምርጫ በማጣጣል በመዋጮ ስም ተላላኪ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ለመሾም ጡረተኛ ፖለቲከኞችን እያሰባሰበች ትገኛለች” ሲሉ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሰው የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ ገልጸዋል።

አቶ ታዬ አሜሪካት የህዳሴ ግድብ እንዳይሞላ ከጠላት ጋር መወገኗን፣ እንዲሁም “ኢትዮጵያን ማፍረስ” ዋነኛ ዓላማው አድርጓል ያሉትን ጁንታው የሚሉትን ሕወሃትን በሞራል እና ቁሳቁስ በመደገፍም ወንጅለዋል።

አክለውም “በኢትዮጵያ ውስጥ የወረዳና የቀበሌ ድንበሮችን ለመወሰን ከጅላለች” ያሉት ታዬ፣ “የኢትዮጵያ ህዝብ በዚሁ ምክንያት ቂም መያዙን” ስለምታውቅ “ቂሙን ለማረሳሳት ከትላንት ወድያ የኮረና ክትባት ለኢትዮጵያ ሰጥቻለሁ ብላ በሚዲያ እንዲወራላት ጠይቃለች” ብለዋል።

አሜሪካ “ኢትዮጵያውያን የመረጡትን ጠልቼ ኢትዮጵያዉያንን እወዳለሁ” ብላለች ያሉት አቶ ታዬ፣ የኢትዮጵያዉያንን ምርጫና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማያከብር ሀገር ለምን እርዳታ ይሰጠናል ሲሉ ጠይቀዋል።

ጨምረውም እኛስ ለምን ከጠላታችን እጅ እርዳታ እንቀበላለን፣ ክትባቱ ራሱ ኮረናን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት የCIA ሴራ አለመሆኑንስ በምን እናውቃለን ብለዋል።

የብልጽግና ሹመኛው አቶ ታዬ “ከሞራልና ከጤና አኳያ” ክትባቱን አለመቀበል ይበጀናል ያሉ ሲሆን፣ በነፃነት መሞት እንደሚበጅ መክረዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img