Monday, October 14, 2024
spot_img

አዲስ ስታንዳርድ ዳግም ሥራ ጀመረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 14፣ 2013 ― በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ፍቃድ መነጠቁን ተከትሎ ሥራ ማቆሙን አሳውቆ የነበረው አዲስ ስታንዳርድ ድረ ገጽ ዳግም ወደ ሥራ መመለሱን እውቁልኝ ብሏል።

ድረ ገጹ ወደ ሥራ የተመለሰው ባሰለፍነው ሰኞ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ኃላፊዎች ጋር ባደረገው ውይይት በኋላ መግባባት ላይ በመደረሱ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ባለስልጣኑ ድረ ገጹን ባገደበት ወቅት አዲስ ስታንዳርድ በኢትዮጵያ ፓርላማ “ሽብርተኛ” ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓት “የትግራይ መከላከያ ሰራዊት” የሚለውን ቃል በመጠቀም የህወሓትን አጀንዳ የሚያራምድ መሆኑን ገልጾ ነበር።

እግዱን በተመለከተ የተናገሩት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ ኢድሪስ፣ ሁለቱ አካላት ባደረጉት ውይይት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img