Monday, October 14, 2024
spot_img

መንግሥት የህወሓት ኃይሎች መንገድ በመዝጋታቸው እርዳታ ማጓጓዝ አልተቻለም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 14፣ 2013 ― የፌደራሉ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይደርስ የህወሓት ኃይሎች መንገድ እየዘጉ ነው አለ።

የፌደራሉ መንግሥት የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በትዊተር ገጹ ላይ ይፋ እንዳደረገው፤ የህወሓት ኃይሎች ባለፉት ሦስት ቀናት ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን ይዘው ወደ ትግራይ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 189 የደረቅ ጭነት መኪኖች ላይ መንገድ በመዝጋት “የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል” ብሏል።

የህወሓት ኃይሎች በአፋር ክልል ዞን አራት፤ ያሎ ወረዳ ፈረንቲሱ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ጥቃት መሰንዘራቸውንም መንግሥት አስታውቋል።

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፤ ባለፉት ሶስት ቀናት በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ክልል በመጓዝ ላይ የነበሩት ከባድ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ በመደረጉ ተሽከርካሪዎች ለመቆም ተገደዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ወደ ትግራይ እርዳታ ጭነው ሲጓዙ በነበሩ አስር ተሽከርካሪዎቼ ላይ ጥቃት ደርሷል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናንት መግለጹ ይታወሳል።

ይህ ጥቃት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት የበለጠ አዳጋች ያደርገዋል ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም አመልክቷል።

ጥቃቱ የደረሰው በአፋር ክልል ከሰመራ ከተማ 115 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ ስፍራ እሁድ ዕለት መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በመግለጫው ማስታወቁን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img