Sunday, October 6, 2024
spot_img

በመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የታገደው የአዲስ ስታንዳርድ ፍቃድ ሊመለስ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሐምሌ 12፣ 2013 ― ባለፈው ሳምንት አጋማሽ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ማኅበር የታገደው የአዲስ ስታንዳርድ ድረ ገጽ ፍቃድ ሊመለስ ተነግሯል።

ድረ ገጹ እግዱን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በዘረዘረበት መግለጫው ይህንኑ አሳውቋል።

አዲስ ስታንዳርድ በመግለጫው በዛሬው እለት ሁለት ባልደረቦቹ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ኃላፊዎች ጋር መምከሩን ያመለከተ ሲሆን፣ በዚሁ ውይይት ወቅት ኃላፊዎቹ ባለሥልጣኑ በአዲስ ስታንዳርድ ላይ በወሰደው የእግድ እርምጃ ሂደት ስህተት መፈጸሙን ማመናቸው ተገልጿል።

በውይይቱ ወቅት ለአዲስ ስታንዳርድ እግድ ሰበብ ሆኗል የተባለው ከሕወሃት ኃይሎች ሥያሜ ጋር ያሉ ጉዳዮች ተነስቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ኃላፊዎች የድረ ገጹ ፍቃዱ በመጪው ረቡዕ እንደሚመለስ አረጋግጠውልኛል ብሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img