Tuesday, November 26, 2024
spot_img

ቀይ መስቀል በትግራይ በቁጥጥር ስር የሚገኙ የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮችን መጎብኘት መጀመሩን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሐምሌ 12፣ 2013 ― ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማሕበር በትግራይ ክልል የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮችን መጎብኘት መጀመሩን አስታውቋል።

ማሕበሩ ትባወጣው መግለጫ ላይ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማሕበር ኦፕሬሽን ኃላፊ ማሪያ ሶሌዳድ ሩኤዳ ጋርሺያ “በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን መጎብኘት ከዋና ኃላፊነቶቻችን መካከል የሚገኝ ሲሆን፣ በአገሪቱም ማሕበሩ ከተቋቋመበት ምክንያት አንዱ ነው። ይህን ቁልፍ እንቅስቃሴ በትግራይ መጀመራችን ደስተኞች ነን” ብለዋል።

ማሕበሩ በትግራይ ክልል በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች አባላትን በተጠናቀቀው ሳምንት መጀመሪያ መጎብኘት ጀመርኩ ከማለት ውጪ የጦር ኃይል አባላቱን ብዛት እና የሚገኙበትን ሁኔታ ግልጽ አላደረገም።

የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የመከላከያ ሠራዊት መቀለን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ ወደ ትግራይ መዲና ከተመለሱ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን መማረካቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረው ነበር።

በትግራይ ኃይሎች የተማረኩ የአገር መከላከያ አባላት ናቸው የተባሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሠራዊት አባላት በኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ ላይ በመቀለ ጎዳናዎች ላይ መታየታቸው ይታወሳል።

ከቀናት በፊት የህወሓት አመራሮች ለሮይተርስ የዜና ወኪል በቁጥጥር ሥር ካዋሏቸው እስረኞች መካከል 1ሺህ የሚሆኑ እስረኞችን ስለመልቀቃቸው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተናግረዋል። ይህ ግን በገለልተኛ አካል አልተረጋገጠም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img