Sunday, September 22, 2024
spot_img

ሕወሃት በምርኮ ይዣለሁ ካላቸው የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች መካከል መልቀቁ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 10፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውና ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ውጊያ ውስጥ የሚገኘው ሕወሃት፣ በምርኮ ይዣለሁ ካላቸው የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች መካከል መለቀቀቁን የሚያመለክቱ የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

ወታደሮቹ ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በተደረገ ስምምነት መለቀቃቸውን ሪፖርቶቹ አመልክተዋል፡፡

በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንዳመለከቱት በርካቶች በአይሱዙ ተጭነው ተጓጉዘዋል፡፡

የወታደሮቹን ጉዳይ በተመለከተ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በይፋ የተሰጠ ማብራሪያ ባይኖርም፣ ከቀናት በፊት የሕወሃት አመራሮች በምርኮ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ይዘናል ባሉበት ወቅት፣ የሠራዊቱ ቃል አቀባይ ኮለኔል ጌትነት አዳነ ቁጥሩ ተጋኗል የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img