Sunday, September 22, 2024
spot_img

አምነስቲ በሲቪሎች ላይ የሚደርስ ሕገ ወጥ እስር እና ጥቃት በአፋጣኝ ይቁም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 9፣ 2013 ― አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ ይደረጋል ያለውን የትግራይ ተወላጆች፣ የአክቲቪስቶች እና የጋዜጠኞች ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር እንዲቆም ጠይቋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የትግራይ ተወላጆች ለእስር ተዳርገዋል ያለው፣ የሕወሃት ኃይሎች የትግራይ ክልል መቀመጫ መቀለን መያዛቸው ከተሰማ በኋላ ነው ያለ ሲሆን፣ እስሩም ማንነትን መሠረት ያደረገ እንደሚመስል ጠቁሟል፡፡

የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች መታሰራቸውን የመብት ተሟጋቹ ድርጅት ገልጿል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ዲፕሮስ ሙቼና ለአምነስቲ ቃላቸውን የሰጡ ከእስር የወጡ የትግራይ ተወላጆች ‹‹እስር ቤቶች ትግርኛ ቋንቋ በሚናገሩ ሰዎች እንደሞሉ›› ተናግረዋል ብለዋል፡፡

አምነስቲ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ታስረው ይገኛሉ ያለ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስርን እንዲያቆም እንዲሁም ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቅ ጠይቋል።

ከሰሞኑ ይታሰራሉ የሚባሉ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ በበኩላቸው፤ ‹‹ሰዎች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ሊውሉ ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ ማንም ሰው ማንነቱን መሠረት ባደረገ መልኩ ለእስር አልተዳረገም›› ሲሉ ለሬውተርስ ተናግረው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img