Tuesday, October 8, 2024
spot_img

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ንብረታቸው እየተዘረፈባቸው መሆኑ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 9፣ 2013 ― በደቡብ አፍሪካ የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ መታሰርን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሁከት ንብረታቸው እየተዘረፈባቸው መሆኑን በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ነግረውጫል ብሎ አል ዓይን ዘግቧል፡፡

የዜና ድረ ገጹ ሥማቸውን ያልጠቀሳቸው የጆሐንስበረግ እና የፕሪቶሪያ ከተሞች ነዋሪዎችን ዋቤ አድርጎ እንደዘገበው፣ በደቡብ አፍሪካ ከተሞች ሁከት ከተከሰተ በኋላ ዛሬ ሰባተኛ ቀኑ ላይ ነው።

እስካሁን ባለው ሁከት አመጽ እስካሁን የ117 ሰዎች ሕይወት ማለፉ የተገለጸ ሲሆን፤ ከ1 ሺሕ 200 በላይ ሰዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሁከቱ ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውን እንዳልሰሙ የተናገሩት ኢትዮጵያውያኑ፣ ንብረቶቻቸው የተዘረፈባቸው እና በእሳት የወደመባቸው ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ግን ገልጸዋል።

በከተሞቹ ንብረት ዘረፋና ወከባ መኖሩን የተናገሩት እነዚህ ነዋሪዎች፣ ሁከቱ የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም ፖሊስ ዘረፋውን እና እሳት አደጋውን ሙሉ ለሙሉ ማስቆም አለመቻሉ ሁከቱ አሁንም ሊቀጥል የሚችል ስጋት እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

በሀገሪቱ የተፈጠረው ሁከት የኢኮኖሚ ዋና ከተማ በሆነችው ጆሃንስበርግ መረጋጋት ቢታይም የሁከቱ ማእከል የነበረችው ደቡባዊዋ ግዛት ኳዋዙል ናታል እስካሁን እንደቀጠለ ነው ተብላል፡፡ ለሁከቱ መነሻ የሆኑት ጃኮብ ዘዙማ ዙማ ለፍርድ ቤት ንቀት አሳይተዋል በሚል ለ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚሁ ጋር በተገናኘ በአገሪቱ የተከሰተው ሁከት የታቀደ መሆኑን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ መናገራቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img