Friday, November 22, 2024
spot_img

አሜሪካ ከ450 ሺሕ በላይ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ከትባት ለኢትዮጵያ ለገሰች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 9፣ 2013 ― አሜሪካ ከ450 ሺህ በላይ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ከትባት ለኢትዮጵያ መለገሷ ተሰምቷል።

ክትባቱ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በስጦታ ያበረከተችው መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ነግሮኛል ብሎ አል ዐይን ዘግቧል፡፡

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የሰጠችው የክትባት አይነት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሆኑ ተገልጧል።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የተሰጣትን ክትባት የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 12፣ 2013 ጧቱ ላይ ከአዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት እንደምትረከብ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ክትባቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የአሜሪካው አምባሳደር በተገኙበት የርክብክብ ፕሮግራሙ ይካሄዳል ተብሏል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አድርጋ ከ277 ሺሕ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፣ 262 ሺህ 200 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

እስከ ትናንት ሐምሌ 8፣ 2013 ድረስ 4 ሺህ 350 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን እንዳጡ የጤና ጥበቃ ዕለታዊ ሪፖርት ያስረዳል።

ኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመከላከል እስካሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች የአስተራ ዘኒካ እና ሲኖ ፋርም የኮሮና ቫይረስ ከተባቶችን የሰጠች ሲሆን የፊታችን ሰኞ ደግሞ የአሜሪካውን ጄ ኤንድ ጄ ክትባት ትረከባለች።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img