Saturday, October 5, 2024
spot_img

ቱርክ ለኢትዮጵያ ድሮን አቅርባለች የሚል የሐሰት ወሬ ተሠራጭቶብኛል አለች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 9፣ 2013 ― ቱርክ ለኢትዮጵያ ድሮን አቅርባለች የሚል የሐሰት መረጃ ተሠራጭቶብኛል ብላለች፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ በትዊተር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው፣ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ቱርክ ለኢትዮጵያ ማቅረቧን በተመለከተ መረጃ መሠራጨቱን በማመልክት፣ መረጃውን ‹‹ሐሰት ነው›› ብሎታል፡፡

የቱርክ ኤምባሲ ማስተባበያ የመጣው በተያዘው ሳምንት አጋማሽ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ለሕወሃት ቅርበት አለው የሚባለው ‹ኤሪትሪያ ሐብ› የተሰኘ ድረ ገጽ፣ አስር ቱርክ ያቀረበቻቸው ድሮኖች በአዲስ አበባ በቱርካዊያን ቴክኒሻኖች እገዛ እየተገጣጠሙ ነው የሚል ዘገባ ማውጣቱን ተከትሎ ነው፡፡

ከስምንት ወራት በፊት የሕወሃት ኃይሎች በሰሜን እዝ ላይ ፈጽመውታል የተባለውን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት የድሮኖች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተነግሮ ነበር፡፡

አሁን ከኢትዮጵያ ጋር በተገናኘ ባልዋልኩበት ሥሜ ተነስቷል ያለችው ቱርክ፣ በአሁኑ ወቅት በድሮን ምርት ታዋቂ እየሆነች መምጧቷ ሲነገር፣ አዘርባጃን ከአርሜንያ ጋር ባደረገችው ጦርነት የቱርክን ድሮን ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅማ ማሸነፏንም መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img