Monday, October 14, 2024
spot_img

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሕወሓት ታዳጊዎችን በጦርነት መማገዱ ሊወገዝ የሚገባው ነው አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 9፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ፍትሕ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሕወሓት ታዳጊዎችን ለወታደርነት እየመለመለ እና ለጦርነት እማገደ መሆኑን የሚያሳዩ ዘገባዎች መውጣታቸውን አመልክተው፣ ይህን የጦር ወንጀል የሆነ ተግባር ሁሉም ሰው ያለምንም ማቅማማት ሊያወግዘው የሚገባ መሆኑን በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ሕወሃት ይህን ተግባር መፈፀሙ አፀያፊ እና ከዚህ በፊት ከሠራቸው ኢሰብዓዊ ድርጊቶች አንፃር አያደርገውም ተብሎ የማይጠበቅ ተግባር መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስለከዋል፡፡

በተለይ ከሰሞኑ የአሜሪካው ኒው ዮርክ ታይምስ የትግራይ ክልልን አስመልክቶ በሠራው ዘገባ እድሜያቸው ከ15 ዓመት የማይዘል የሚመስሉ ሁለት ታዳጊዎች ኤኬ 47 የተሰኘውን ጠመንጃ አንግበው በሌሎች ታዳጊ ሕፃናት ተከበው ሲራመዱ እንዲሁም፣ በሌላኛው ፎቶ ጉዳት የደረሰበት የሚመስል ሰው በቃሬዛ ተሸክመው የሚሄዱ ሰዎችን ሁለት ኤኬ 47 አንግቦ የሚጓዝ ታዳጊን የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ አያይዞ ጉዳዩ በርካቶችን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት በትግራይ ክልል ጉዳይ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ‹‹አሁን ባለው ቁመናው ያለ ግጭት ውሎ ማደር አይችልም›› ያሉት ሕወሓት፣ ‹‹ሕፃናት እና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል›› ብለው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img