Monday, October 14, 2024
spot_img

የአማራ ክልል በሕወሓት የተወረሩብኝን አካባቢዎች እያስመለስኩ እገኛለለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሐምሌ 8፣ 2013 ― የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ዛሬ ነግረውኛል ብሎ ዶይቼ ቬሌ እንደዘገበው የአማራ ክልል ኃይሎች ከትላንት ጀምሮ ባደረጉት መልሶ ማጥቃት “የሕወሓት ወራሪ” ያሉት ቡድን ወደቦታው ተመልሷል ብለዋል፡፡

ወረራው በአማራ ክልል ተወስኖ እንደማይቀር የታወቀ በመሆኑ፣ ክልሎች ወራሪውን ለመዋጋት እየተቀላቀሉ ነው በማለት ጨምረው ተናግረዋል፡፡

እስካሁንም የኦሮሚያና የሲዳማ ልዩ ኃይል አባላት መቀላቀላቸውንም አመልከተዋል፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካንና የሌሎችንም ምዕራባውያን አገሮች አድሎአዊ አተያይ ያሉትን አቶ ግዛቸው ኮንነዋል።

ባለፉት ቀናት ግዛት አስመልሳለሁ በሚል የሕወሓት ኃይሎች አድርገውታል በተባለ ዘመቻ የአላማጣ እና ኮረምን አካባቢዎች መያዛቸውን ተናግረው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚሁ አካባቢ በአሁኑ ሰዓት ጦርነት እየተካሄደ ስለመሆኑ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img