አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንቶኒ ብሊንከን ዓመታዊ የዘር ማጥፋት እና የጭካኔ መከላከል ሪፖርት ሲያቀርቡ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል ከተባሉ ስድስት አገራት መካከል ኢትዮጵያን ጠቅሰዋል።
በሪፖርቱ ከኢትዮጵያ ተጨማሪ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል የተባሉት ሃገራት በርማ በመባል የምትታወቀው ማይናማር፣ ቻይና፣ ኢራቅ ሶሪያ እና ደቡብ ሱዳን ሆነዋል።
ሚኒስተሩ በነዚህ አገራት ለውጥ ለማምጣት “በዲፕሎማሲ፣ በውጪ ሃገር እርዳታ፣ እውነታውን በማፈላለግ ተልዕኮ፣ በገንዘብ፣ በተሳትፎ ድጋፍ እና ይህን በመስሉ እጃቸን ላይ ባሉ የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ተጽእኖ እና ምላሽ መስጠት የሚረዱ ሪፖርቶችን በማውጣትም ባለው ነገር ሁሉ እንጥራለን” ብለዋል፡፡
አሜሪካ በጥቅምት ወር የተቀሰቀሰውን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል ስትል ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ስታወጣ መሰንበቷ ይታወቃል።