Friday, November 22, 2024
spot_img

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ትግራይ ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ሁኔታ አሳስቦኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ትግራይ ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች የሚገኙበት ሁኔታ እንዳሳሰበው ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዴ ትግራይ ውስጥ የኤርትራ ስደተኞች በሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎች አቅራቢያ ውጊያ እና ተኩስ መኖሩ አዲስ መረጃ መስማታቸው እጅግ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

በክልሉ የሚገኙት ኤርትራዊያን ስደተኞች በአሁኑ ወቅትም ላለፉት ወራት በትግራይ ውጊያ ሲካሄድ ለአንዱ ወግናችኋል በሚል የበቀል ጥቃት፤ እገታ፣ እስር እና ጥቃት በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ መሆኑን ተአማኒ እና የተረጋገጠ ዘገባ ድርጅቱ እንደደረሰውም የኮሚሽነሩ መግለጫ ዘርዝሯል።

በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እና ማዋከብ መቆም እንዳለበት ያሳሰበው የኮሚሽነሩ መግለጫ፣ ስደተኞች ሲቪሎች መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥቶ ዓለም አቀፍ ከለላ የማግኘት መብት እንዳላቸውም አመልክቷል።

በተለይም ማይ እኒ እና አዲ ሀሩሽ በተባሉት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች በምሽት አጠቃላይ የወንጀል ድርጊቶች እንደሚፈጸሙ መሰማቱ እንደረበሻቸውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img