Monday, October 14, 2024
spot_img

የአላማጣ ከንቲባ በከተማው ነዋሪዎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና ዘረፋ እየተፈፀመባቸው ነው ማለታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አንስቶ በፌደራሉ መንግስት የተላለፈውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ተከትሎ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች አላማጣ ከተማ ስለመግባታቸው ተነግሯል፡፡

ከተማዋ ውስጥ ከገቡም በኋላ ነዋሪዎቹን እየገደሉና እዘረፉ ነው ሲሉ ከንቲባው አቶ ካሳ ረዳ ነግረውናል ብሎ አሻም ቲቪ ዘግቧል፡፡

ከንቲባው እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ሐምሌ አምስት ቀን 2013 ዓ.ም አላማጣ ከመግባታቸው አስቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሀይልና ሚሊሻዎች ከተማዋን ለቅቀው ወጥተዋል፡፡

ከትግራይ ክልል ታጣቂዎች ከተማዋን ከረገጡበት ዕለት ጀምሮ የአላማጣ ነዋሪዎችን እየገደሉ ነው፤ ሀብት እየዘረፉ፣ ንብረቱን እያወደሙ ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ከንቲባው ይህ የተደራጀ ወንጀል እንዲቆም የአማራ ክልልንም ሆነ የፌደራሉን መንግስት ዕርዳታ ብንጠይቅም ምላሽ አላገኘንም ማለታቸው ተመላክቷል፡፡

የሕወሃት ኃይሎች ጀምረውታል የተባለውን የግዛት ማስመለስ ጦርነት ተከትሎ በትላንትናው እለት አላማጣ እና ኮረምን መቆጣጠራቸው መነገሩ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img