Sunday, September 22, 2024
spot_img

አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ዴልታ በኢትዮጵያ ስለመከሰቱ ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ዴልታ በኢትዮጵያ ስለመከሰቱ ጥናት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ አልፋ እና ቤታ የተሰኙ የቫይረሱ ዝርያዎች መኖራቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ የዴልታ ዝርያ ስለመኖሩ ለማረጋገጥ ስራዎች መጀመራቸውም ሚንስትሯ ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በጤና ተቋማት መሰጠት ይጀምራል።

በኢትዮጵያ ከ277 ሺሕ በላይ ዜጎች ኮቪድ-19 ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን 4 ሺሕ 343 ሰዎች ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ለሞት ተዳርገዋል።

በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኮቪድ ክትባት ከወሰዱ ሶስት ወር የሞላቸው ዜጎች ከነገ ጀምሮ እንደሚከተቡ እና በክልሎች ደግሞ ክትባቱን ከሐምሌ 9፣ 2013 ጀምሮ መውሰድ እንደሚቻል ሚኒስትሯ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር እየሰራ ነው ያሉት ዶ/ር ሊያ፤ 400 ሺሕ የአስትራዜኒካ ክትባት ለሁሉም ክልሎች እየተሰራጨ መሆኑን አክለው ጠቅሰዋል።

በቀጣይም 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ የጠቀሱት ሚኒስትሯ የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞች፣ ፖሊሶች፣ መምህራን፣ የባንክና የፍርድ ቤት ሰራተኞች፣ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸው እና በእድሜ የገፉ ዜጎች እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞች የመጀመሪያውን ዙር ክትባት እንዲወስዱ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

የመጀመሪያ ዙር ክትባት የሚወስዱ ዜጎች ሁለተኛው ዙር ክትባት ከ3 እስከ 4 ሳምንት ስለሚሰጥ ዜጎች ክትባቱን እንዲወስዱም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውሰዋል። የኮቪድ- 19 ምርመራን በተመለከተም በ20 ደቂቃ የሚያደርስ ፈጣን ምርመራ ማድረጊያ መሳሪያ ለክልሎች መሰራጨቱን መጠቆማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img