Monday, October 14, 2024
spot_img

ዶክተር አርከበ እቁባይ ለተመድ ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተነት ሳይመረጡ ቀሩ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሐምሌ 6፣ 2013 ― ዶክተር አርከበ እቁባይ ለተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተነት ሳይመረጡ ቀርተዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ላይ የካበተ ልምድ እንዳላቸው የሚታመንባቸው፣ የጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆንና በተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የኃላፊነት ስራዎች ላይ ያገለገሉት ዶዶክተር አርከበ፣ ከጀርመኑ ገርድ ሙለር እና ከቦልቪያው በርናንዶ ካልዛዲላ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ነበር፡፡

ቀድሞ በነበረው ሁኔታ ፉክክሩን አሸንፈው እንደሚመረጡ የብዙዎችን ቅድመ ግምት አግኝተው የነበረ ቢሆንም፣ እንደታሰበው ሳይመረጡ ቀርተዋል፡፡

በምርጫው ሂደት የጀርመን የፌዴራል የምጣኔ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ገርድ ሙለር ቀጣዩ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ሙለር በዋና ዳይሬክተርነት የተመረጡት በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ቦርድ አማካኝነት ነው፡፡

የቦርዱ ምርጫ የድርጀቱ ከፍተኛ አካል በሆነውና እንደፈረንጆቹ ኅዳር 29 እስከ ታኅሣሥ 3፣ 2021 በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ይጸድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡

ሙለር በፈረንጆቹ ከ2013 አንስቶ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትን ሲመሩ የቆዩቱን ቻይናዊው ሊ-ዮንግን እንደሚተኩ የአል ዓይን ዘገባ አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img