Monday, October 14, 2024
spot_img

አሜሪካ ቀድሞ የነበረውን የክልሎች ድንበር በኃይል መዳፈር ተቀባይነት የለውም አለች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሐምሌ 6፣ 2013 ― የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ቀድሞ የነበረውን የክልሎችን ድንበር በኃይል መዳፈር ተቀባይነት የለውም ሲል አሳስቧል፡፡ ስቴት ዲፓርትመንት በመግለጫው በአሁኑ ወቅት በምዕራብ ትግራይ ወታደራዊ ግጭት የሚያባብስ ሁኔታ እንዳለና ይኸው እጅጉን አሳሳቢ መሆኑን አንስቷል፡፡

በመሆኑም በመግለጫው የትግራይ መከላከያ ኃይል የተባለው የሕወሃት ኃይል፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን አንድነት በሚጠብቅ እና የዜጎችን ደኅንነት በጠበቀ መልኩ ወደ ተኩስ አቁም እንዲያመሩ ጠይቋል፡፡

መግለጫው በትግራይ ክልል በተደራጁ ታጣቂዎች፣ በጸጥታ አካላትም ሆነ በሌሎች የሚደረግን የንጹሐን ጥቃት የኮነነ ሲሆን፣ በአገሪቱ የታጠቁ ኃይሎች ከንጹሐን ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንዲያከብሩ ጠይቋል፡፡ ፡፡

አክሎም ከንጹሐን ጥቃት ጋር በተገናኘ አጥፊዎች ተጠያቂ የሚደረጉበት ሁኔታ እንዲኖር ተጠይቋል፡፡

የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት መግለጫ ከድንበር ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ኢትዮጵያውያን በጋራ ስምምነት እንጂ በጠብመንጃ የሚፈቱት አይደለም ብሏል፡፡

የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት መግለጫ የወጣው ከባለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ በምዕራብ ትግራይ በአሁኑ ወቅት በአማራ ልዩ ኃይል ቁጥጥር ስር በዋሉ አካባቢዎች በሕወሃት ኃይሎች እና በአማራ ልዩ ኃይል መካከል የጦርነት ዝግጅት መኖሩ በሥፋት እየተነገረ ባለበት ወቅት ነው፡፡

ይህንኑ የሕወሃት መሪዎችም ሆነ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ባለሥልጣናት ሲያስተጋቡት ተደምጠዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img