Sunday, September 22, 2024
spot_img

በሱማሌ ክልል ንግድ ባንክ ከ20 ሺሕ ብር በታች መላክ አትችሉም በማለቱ ቅሬታ ቀረበበት

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሐምሌ 5፣ 2013 ― በሱማሌ ክልል ቶጎ ጫሌ አካባቢ የሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ከ20 ሺሕ ብር በታች መላክ አትችሉም በመባላቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው የሚገኙ ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ከሰኔ 28፣ 2013 ጀምሮ በክልሉ ከሚገኝ ንግድ ባንክ ወደ አዲስ አበባ ከ20 ሺሕ ብር በታች ገንዘብ መላክ አትችሉም መባላቸውን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ሰምቻለሁ ብሏል፡፡

የገደቡ ምክንያት ምን እንደሆነ በግልጽ የተነገረን ነገር የለም የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ከቶጎ ጫሌ ወደ አዲስ አበባ ገንዘብ ማስተላለፍ አልቻልንም ብለዋል። እንደ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከሆነ ቶጎ ጫሌ አካባቢ የዶላር ምንዛሬ በስፋት ስለሚካሄድ ወደ አዲስ አበባ ገንዘብ የሚላከው ዶላር ከተመነዘረ በኋላ በመሆኑ ላኪዎች ከመነዘሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ተቸግረዋል።

ጋዜጣው አነጋገርኳቸው ያላቸው የክልሉ ኃላፊዎች፣ በአሁኑ ሰዓት በምን ምክንያት ይህ አገልግሎት እየተተገበረ መሆኑን ሊረዱ አለመቻላቸውን ገልጸው፣ የግለሰቦችን ቅሬታ ባንኩ በተገቢው መንገድ መፍታት እንደሚገባውም ጠቁመዋል።

በጉዳዩ ላይ አዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ያለወ ነገር የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img