Sunday, October 13, 2024
spot_img

በቦሌ አካባቢ ሁለተ ሆቴሎች ‹‹ሁከት ቀስቃሽ ሙዚቃዎችን›› ከፍታችኋል በሚል በመጠርጠራቸው እንደታሸጉ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሐምሌ 5፣ 2013 ― በአዲስ አበባ ከተባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለመደው አጠራር ቦሌ አካባቢ ከኤድና ሞል ዝቅ ብለው የሚገኙት ሐርመኒ እና ካሌብ ሆቴሎች ‹‹ሁከት ቀስቃሽ ሙዚቃዎችን›› በመክፈት በመጠርጠራቸው መታሸጋቸው ተሰምቷል፡፡

ሆቴሎቹ የታሸጉት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ትዕዛዝ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ፎርቹን ይዞት የወጣው ዘገባ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ ከ70 በላይ የሚሆኑ በዚያው ክፍለ ከተማ በተለመደው አጠራር ሃያ ሁለት ማዞሪያ እና ቦሌ አካባቢ የሚገኙ የመሸታ ቤት እና ሬስቶራንቶች ታሽገዋል ተብሏል፡፡

የታሸጉት ሆቴሎች እና መሸታ ቤቶች በቅርቡ የሕወሓት ኃይል ወደ መቐለ ከተማ መመለሱን ተከትሎ የተጠቀሰውን ሁከት ቀስቃሽ ድርጊት መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img