Friday, November 22, 2024
spot_img

ሕወሓት በምርኮ ይዣለሁ ያላቸው ወታደሮች የቪዲዮ-ምስል በፎቶ ሾፕ የተቀናበረ ነው ሲሉ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሐምሌ 5፣ 2013 ― ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል ዋና መቀመጫ መቐለ ከተማ የተመለሰው የሕወሓት ኃይል በምርኮ ይዣቸዋለሁ ብሎ የለቀቀው የአገር መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች የቪዲዮ-ምስል በፎቶሾፕ የተቀናበረ ነው ሲሉ የመከላከያ ሠራዊት የግንባታ ሥራዎች ኃላፊው ሌተናል ባጫ ደበሌ ትናንተ ከወጣቶች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ተናግረዋል፡፡

ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ በዚሁ በመንግሥት ሚዲያዎች በተላለፈው ንግግራቸው፣ ሕወሓት ያሳየው የቪዲዮ ምስል ከሌላ ሀገር ታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ ምስል በመውሰድ በቅንብር ‹‹ሬንጀር አልብሰው›› ያሳዩት ነው ሲሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አክለውም ለተሰበሰቡት ሰዎች ድሮም ውሸታሞች ናቸው ያሏቸው ሕወሓቶችን፣ ‹‹ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከፌስቡክም ሆነ ከሌላ ማንኛውም ቦታ የእነሱን [መረጃ] ዐይቶ ላለማመን ወስኑ›› ሲሉ ታዳሚውን ሲጠይቁ፣ ከታዳሚው በጭብጨባ ምላሸ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የሕወሓት ኃይሎች በምርኮ ይዣለሁ ያላቸው የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮችን በተመለከተ የተለያዩ ቁጥሮች ሲነገር የቆየ ሲሆን፣ ከሕወሓት አመራሮች መካከል በኒውዮርክ ታይምስ በጽሑፍ ቃለ ምልልሳቸው የታተመው ዶክተር ደብረጽዮን 6 ሺሕ ወታደሮችን ማርከናል ሲሉ፣ ጦሩን ይመራሉ የሚባሉት ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ በበኩላቸው 8 ሺሕ ወታደሮችን እንደማረኩ ለሬውተርስ የዜና ወኪል ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከዚህ ቀደም ለሚዲያዎች ማብራሪያ የሰጡት የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነቱ ተጠሪ ኮለኔል ጌትነት አዳነ ቀጥሩ የተጋነነ መሆኑንና ምርኮውን በተመለከተም፣ በርካታ መካከለኛ እና የበታች ወታደሮች ሕዝብ ላይ አንተኩስም በሚል አቋም ያደረጉት ነው ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒፎርም የለበሱ ምርኮኛ ወታደሮችን የሚያሳዩ የቪዲዮና የፎቶ ምስሎች በኒው-ዮርክ ታይምስ እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ከተለቀቁ ወዲህ ጉዳዩ በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img