ምርጫ ቦርድ ዛሬ ይፋ ባደረገው የምርጫ ውጤት መሠረት ብልጽግና ፓርቲ ምርጫ ከተደረገባቸው 436 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ 410 መቀመጫ ማግኘቱን አስታውቋል።
በሌላ በኩል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን 5 የህዝብ ተወካች ምክር ቤት መቀመጫዎች ማግኘቱንም ቦርዱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ደግሞ 4 የህዝብ ተወካች ምክር ቤት መቀመጫዎች ማግኘቱን ነው ቦርዱ ገልጿል።
የጌዲዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትም 2 የህዝብ ተወካች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ማሸነፉን ማግኘቱንም ነው ቦርዱ ያስታወቀው።