Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ለቦይንግ 737 ማክስ አደጋ ተጎጂ ቤተሰቦች የካሳ ገንዘብ መከፋፈል መጀመሩ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 3፣ 2013 ― በመጋቢት ወር 2011 በኢትዮጵያ እንዲሁም ከዚያ ቀድሞ በኢንዶኔዥያ በተከሰከሰው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ተጎጂ ቤተሰቦች የተወሰነው 500 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ገንዘብ መከፋፈል መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

ይኸው የካሳ ገንዘብ ለጉዳዩ ዕልባት ለመስጠት የአሜሪካ ፍትሕ መስሪያ ቤት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር በመነጋገር ገንዘቡ ጉዳቱ ለደረሰባቸው ለኢንዶኔዥያ ላየን ኤር እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ተጎጂ ቤተሶቦች እንዲሁም ሕጋዊ ወራሾች የሚከፋፈል ነው፡፡

ለቦይንግ ማክስ 8 737 የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች ኩባንያው 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የካሳ ክፍያ እንዲፈጽም ከዚህ ቀደም መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በሁለቱ የአውሮፕላን አደጋዎች በአጠቃላይ የ346 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ በጉዳት ካሳው ለእያንዳንዱ ጉዳዩን ኪን ፊንበር እና ካሚሊ ቢሮስ በተባሉ የሕግ ቢሮዎች በኩል ለሚከታተሉ የተጎጂ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 1 ነጥብ አራት አምስት ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ነው ኩባንያው የተስማማው፡፡

አደጋውን ካስተናገዱት የቦይንግ አውሮፕላኖች መካከል ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ለስድስት ደቂቃዎች በኋላ አየር ላይ ከቆየ በኋላ የተከሰከሰው በመጋቢት ወር 2011 ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img