Saturday, October 5, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ቀውስ ጉዳይ አጀንዳ ይዞ እንዲነጋገር ሂዩማን ራይትስ ዎች አሳሰበ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 3፣ 2013 ― የተባሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ቀውስ ጉዳይ አጀንዳ ይዞ እንዲነጋገር የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዎች አሳስቧል፡፡

በትግራይ ክልል ስለደረሱ ከባድ የመብት ረገጣዎች ሪፖርቶች መውጣታቸውን ቀጥለዋል ያለው ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ ጉባኤ ላይ ያለው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዐዊ መብት ኮሚስን ጉዳዩን አጀንዳ ይዞ መነጋገር አለበት ይህን ደግሞ በአስኳይ ሊያደርገው ይገባል ብሏል።

ትግራይ ውስጥ ተፈጽመዋል በተባሉት የሰብዐዊ መብት ረገጣዎች ዙሪያ በአሁኑ ወቅት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዐዊ መብት ከፍተኛ ኮምሽነርን ጨምሮ፣ በአገር ውስጥ፣ በአህጉራዊ እና ዐለም አቀፋዊ ተቋማት የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች ግን የተመድ የሰብዐዊ መብት ከፍተኛ ኮምሽነር የምርመራቸውን ውጤት ለምክር ቤቱ ጉባዔ እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ ውሳኔ ካልተላለፈ በስተቀር ምክር ቤቱ በምርመራው ውጤት ላይ ሊነጋገር አይችልም ብሏል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የምርመራው ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ለሰብዐዊ መብት ምክር ቤቱ አስታውቋል የተባለ ሲሆን፣ የምርመራው ውጤት አሁን ባለበት ደረጃ ላይ ለመነጋገር የሚፈቅድ ውሳኔ ከተላለፈ ግን የሂደቱን ተዓማኒነት ይጎዳል ሲል አሳስቧል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች በበኩሉ አሁን ካለው የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ እና የመገናኛ እና የተደራሽነት ገደቦች አኳያ ምክር ቤቱ ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ማግኘት እና የጭካኔ አድራጎቶች እንዳይቀጥሉ የመከላከል ኃላፊነቱነን ለመወጣት እንዲችል የቀረበውን ውሳኔ ማጽደቅ ይኖርበታል ማለቱን የዘገበው ቮይስ ኦፍ አሜሪካ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img