Monday, October 7, 2024
spot_img

ለሕወሃት ሎቢ አድራጊነት ሲሠራ የቆየው የአሜሪካው ቮንባተን ሞንትግዩ ዮርክ የኦሮሞ እና የትግራይ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ዘመቻን ተቀላቀለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 3፣ 2013 ― ባለፉት ወራት ለሕወሃት ሳደርግ የቆየሁት የሎቢ ሥራ፣ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የቪዛ ማእቀብ በመደረጉ ሥራዬን አሳክቻለሁ ብሎ የነበረው የአሜሪካው ሎቢ አድራጊው ቮንባተን ሞንትግዩ ዮርክ፣ አሁን ደግሞ የኦሮሞ እና የትግራይ ፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚለውን ዘመቻ ተቀላቅሏል፡፡

ይኸው የሎቢ አድራጊ ከዚህ ቀደም በትግራይ ጉዳይ ትግራይ ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ኤንድ ኮሚኒኬሽን በተሰኘ መቀመጫውን አሜሪካ አሌክሳንድሪያ ባደረገ ድርጅት ተቀጥሮ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ የተሰጠኝን ሥራ አሳክቻለሁ ካለ በኋላ የሕወሃት አክቲቪስቶች ውሉ መራዘሙ ግድ ነው የሚል መልእክት ሲያስተጋቡ ታይተው ነበር፡፡

አሁን ለኦሮሞ እና ለትግራይ የፖለቲካ እስረኞች የሚደረገውን ዘመቻ መቀላቀሉን ይፋ ያደረገው ሎቢ አድራጊ በማን እንደተቀጠረ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ ባለፉት ቀናት በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕወሃት መሪዎች ጋር ሊደራደር እንደሚገባ እና አሜሪካ ተጽእኖዋን እንድታሳርፍ የሚሉ ተደጋጋሚ መልእክት አስተጋብቷል፡፡

ከዚሁ ከሎቢ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምንም እንኳ ከወራት በፊት በፓርላማ ተገኝተው የሎቢን ሥራን ያጣጣሉት ቢሆንም፣ የሚመሩት የፌዴራሉ መንግሥት ዋሺንግተን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ቬናብል የተሰኘ በወር 35 ሺሕ ዶላር የሚያስከፍል የሎቢ ድርጅት መቅጠሩ ሲነገር ሰንብቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img