Sunday, October 6, 2024
spot_img

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ እጃቸውን ለፖሊስ ሰጡ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሐምሌ 1፣ 2013 ― ጃኮብ ዙማ በስልጣን ዘመናቸው የሙስና ወንጀልን ፈጽመዋል በሚሉ ተደራራቢ ወንጀሎች መከሰሳቸው የሚታወስ ነው።

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ለፖሊስ እጅ መስጠታቸው ተሰምቷል።

ለፍርድ ቤቱን ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው ዙማ እጄን ለፖሊስ እጅ አልሰጥም ሲሉ መቆታቸው ይታወቃል።

ጃኮብ ዙማ በህግ ቁጥጥር ስር የሚውሉበት ቀን እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ዙሪያ ለተሳበሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው መብታቸው መጣሱን መናገራው ይታወሳል።

ፖሊስ ፕሬዝዳንቱ እጃቸውን ለፖሊስ እንዲሰጡ ቀነ ገደብ አስቀምጦ የነበረ ሲሆን፤ ቀነ ገደቡም ትናነት እኩለ ሌሊት ላይ ነበር የሚጠናቀቀው።

ፕሬዘዳንቱ የሚታሰሩ ከሆነ ደጋፊዎቻቸው በደቡብ አፍሪካ አመጽ እናስነሳለን በማለትም ሲዝቱ ቆይተዋል።

በመጨረሻም ትናንት ምሽት ተፈረደባቸውን የእስር ጊዜ ለመጀመር ትናት ምሽት ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተሰምቷል።

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በትናትናው እለት በካዋዙሉ ናታለ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወስዶ ወደ ማረፊ ቦታ አድርሷቸዋል።

የ79 ዓመቱ ቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤት ለሚያደርገው የሙስና ወንጀል ምርመራ መረጃ ለመስጠት ሲጠየቁ በተደጋጋሚ ባለመተባበራቸው፣ ለፍርድ ቤቱን ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር ተላልፎባቸው ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img