Monday, October 7, 2024
spot_img

የአማራ ልዩ ኃይል በያዛቸው አካባቢዎች ጦርነት እያንዣበበ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 30፣ 2013 ― ባለፉት ቀናት በትግራይ እና በአማራ ኃይሎች መካከል የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች እያመለከቱ ይገኛሉ፡፡

ጦርነቱ ያንዣበበው በትግራይ ጦርነት ወቅት በአማራ ልዩ ኃይል ቁጥጥር ስር በዋሉ አካባቢዎች መሆኑን ነው መረጃዎቹ የሚያመለክቱት፡፡

ለዚሁ ከአማራ ክልል ጎንደር እንዲሁም ከደብረ ማርቆስ እና ሌሎችም አካባቢዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ሚሊሻዎች ወደ ሥፍራው እያቀኑ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በአካባቢው የጦርነት አዝማሚያ መኖሩን በተመለከተ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዎች በትላናትናው እለት በድረ ገጹ ላይ ስጋቱን ገልጾ ነበር፡፡

በትግራይ በኩል ያለውን ሁኔታ በተመለከተም የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ይዞት በወጣ ዘገባ የሕወሃት ኃይሎች በርካታ ሺሕ ወጣቶችን ወደ ምእራብ አቅጣጫ አዝምተዋል፡፡ በትላንትናው እለት ለሚዲያዎች የተናገሩት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ከሕወሃት በኩል ሊሰነዘር የሚችል ጥቃት ለመመከት ተዘጋጅተናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከሳምንት በፊት የመከላከያ ሠራዊት የትግራይ ክልልን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ የክልሉን መቀመጫ መቐለን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን የተቆጣጠሩት የሕወሃት ኃይሎች ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ ጠላት ያሏቸው ኃይሎችን ለመፋለም ወደ አማራ ክልልም ሆነ ወደ ኤርትራ ድረስ እንዘልቃለን ማለታቸው መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img