Sunday, September 22, 2024
spot_img

የሕዳሴ ግደብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት የግብጽን የአክሲዮን ገበያ እንዲቀዛቀዝ ማድረጉ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 30፣ 2013 ― የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት መጀመሩ የግብጽ አካክሲዮን ገበያ እንዲቀዛቀዝ ማድረጉ ተነግሯል፡፡
የግብጽ ዋና የአክሲዮን ገበያ መረጃ ማክሰኞ ዕለት ሁለት በመቶ ያህል የቀነሰ ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያቱ ሁለተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት መጀመሩ ነው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ትናንት ኢትዮጵያ የግድቡን ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት መጀመሯ በግብጽ በኩል የተነገረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌት መጀመሯ የቀጠናውን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ስትል እርምጃውን ግብጽ ተቃውማ ነበር።

የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር መሐመድ ዐብደል አቲ ከኢትዮጵያ በኩል የውሃ ሙሌቱ ስለመጀመሩ የሚገልጽ ይፋዊ ደብዳቤ እንደደረሳቸው አመልክተው ውሳኔውን ግን አንቀበለውም ብለዋል፡፡

እንደ ሬውተርስ የዜና ወኪል ከሆነ የግብጽ ዋና የአክሲዮን ገበያ መረጃ ጠቋሚ 10 ሺሕ 155 ነጥቦችን ወይም 1 ነጥብ 80 በመቶ መቀነሱን አመልክቷል፡፡

የስሪ ዌይ ብሮከሬጅ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ራኒያ ያኩብ ‹‹የሚከናወኑት የባለሐብቶች ግብይቶች የፍርሃት ናቸው። ከህዳሴው ግድብ [የውሃ ሙሌት] በስተቀር ለውድቀቱ ሌሎች ምክንያቶች የሉም›› ማለታቸውንም የቢቢሲ አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img