Sunday, November 24, 2024
spot_img

ጊቤ የተሰኘችው የኢትዮጵያ መርከብ በበርበራ ወደብ አገልግሎት መስጠት ጀመረች

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 30፣ 2013 ― ‹‹ጊቤ›› በሚል ሥያሜ የምትታወቀው የኢትዮጵያ መርከብ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶማሌ ላንድ በርበራ ወደብ መደበኛ የጭነት አገልግሎት መስጠት መጀመሯን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡

መርከቧ ‹‹ገልፍ ኢንዲያ ሰብ ኮንቲነንት›› ከሚባለው አካባቢ 11 ሺሕ 200 ቶን ስኳር እና ሩዝ በመጫን ከትላንት በስትያ በርበራ ወደብ ደርሳለች።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት መርከብ የሆነችው ‹‹ጊቤ›› ወደ ሥፍራው ስትገባ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ፣ በሶማሌ ላንድ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ሰኢድ መሐመድ ጅብሪል እና ሌሎች የሚመለከታቸው የዱባይ ፖርትስ ወርልድ (ዲፒ ወርልድ) የወደብ አስተዳደር ኃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ መርከብ በበርበራ ወደብ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ድርጅቱ ገልጿል።

የበርበራ ተርሚናል ኮርደር የመጀመሪያ ዙር ማስፋፊያ ፕሮጀክት 500 ሺህ ኮንቴነሮችን መያዝ የሚችል ተርሚናል እንደሆነና በዓመት አንድ ሚልዮን ኮንቴነሮችን ማስተናገድ እንደሚችል ተነግሮለታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img