Sunday, September 22, 2024
spot_img

መንግሥት የዐረብ ሊግ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበል ለጸጥታው ምክር ቤት አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 29፣ 2013 ― የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሕዳሴ ግድቡን አስመልክቶ የዐረብ ሊግ ለፀጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ የላከውን ደብዳቤ በማስመልከት ጣልቃ ገብነቱ እንዳሳዘናቸው በትላንትናው እለት ደብዳቤ ልከዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አቶ ደመቀ በደብዳቤያቸው የዐረብ ሃገራት ሊጉ የግብጽን ማናቸውንም ፍላጎቶች ያለ ገደብ እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ድጋፍ በመስጠት እንደሚታወቅ አመልክተዋል።

አክለውም ለኢትዮጵያ፣ ለግብጽ እና ሱዳን የጋራ ድርጅት የሆነው የአፍሪካ ኅብረት ሃገራቱ ተደራድረው «ለአፍሪካዊ ችግር የአፍሪቃ መፍትሔ» በሚለው መርኅ፣ ሁሉም አሸናፊ የሚሆኑበት የጋራ ውጤት ላይ ለመድረስ የሦስትዮሽ መድረክ ማመቻቸቱንም ጠቅሷል።

ሆኖም የግድቡ ድርድር በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት በመካሄድ ላይ እያለ የሊጉ ይሄን መሰሉ አካሄድ ኅብረቱ እና የዐረብ ሊግ ያላቸውን ወዳጅነት እና ትብብር ከግምት እንዳላስገባም በደብዳቤው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በሦስትዮሽ ድርድሩ በቅንነት እየተሳተፈች መሆኑን የገለጸው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ አያይዞም፣ በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት የሚካሄደው ድርድር ስኬታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን በማመልከት፤ ሁለቱ የታችኛው ተፋሰስ ሃገራት በኅብረቱ አማካኝነት ለሚካሄደው ድርድር ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህ አጋጣማሚ ኢትዮጵያ በድጋሚ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሱዳን እና ግብጽ ድንበር ዘለል የውኃ ምንጮች አጠቃቀምን በተመለከተ ተቀባይነት ላለው ዓለም አቀፍ ሕግ ተገዢ እንዲሆኑ እንዲያበረታታም ተጠይቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img