Friday, November 22, 2024
spot_img

በትግራይ ያሉ ስደተኞችን የተመለከቱ ሪፖርቶች አሳሳቢ መሆናቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 29፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጄንሲ በትግራይ ክልል የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ጥቃት ደርሷል የሚል ሪፖርት መውታቱን ጠቁሞ እንዳሳሰበው ገልጧል፡፡

የኤጀንሲው የኢትዯጰያ ቃል አቀባይ በምዕራባዊው የሽረ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ተገድለዋል የሚሉ ሪፖርቶችን ‹‹በኦንላይን እና ከሌሎች ምንጮች›› መረዳታታቸውን ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

«እነዚህን ዘገባዎች በአንክሮ የምንመለከታቸው ሲሆን ሪፖርቶቹን እንደሰማንም ወዲያውኑ በሽረ የሚገኙ ሠራተኞቻችንን፣ አጋሮቻችንን እና ኤርትራውያን ስደተኞችን ለማግኘት ሞክረናል» ሲሉ ኔቨን ክሬቨንኮቪክ ገልጸዋል።

«እስካሁን እየደረሱን ያሉ ማናቸውንም ክሶች ማረጋገጥ ባንችልም የዘገባዎቹን ትክክለኛነት ለመገምገም የሚረዱ ተገቢ መረጃዎችን መሰብሰባችንን እንቀጥላለን» ሲሉ ቃል አቀባዩ አክለዋል።

የመብት ተሟጋቾች በርካታ ኤርትራዊያን ስደተኞች በአካባቢው ባሉ ሚሊሻዎች በጭካኔ መገደላቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች ደርሰውናል ሲሉ እየገለጹ እንደሚገኙም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ባለፈው ሳምንት የአገር መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ በክልሉ ሁሉም የግንኙነት አማራጮች መጥፋት ሪፖርቶቹን ለማረጋገጥ ከባድ አድርጎታል።

በጥቅምት መጨረሻ በትግራይ ክልል ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት 100 ሺሕ የሚጠጉ ኤርትራዊያን በስደተኞች በክልሉ ባሉ ካምፖች ውስጥ እንደነበሩ ይነገራል፡

በጦርነቱ መቀስቀስ በነበሩ አራት ካምፖች መካከል ሁለቱ በኋላ መውደማቸው የታወቀ ሲሆን፣ በካምፖቹ ተጠልለው ከነበሩት ከ20 ሺሕ በላይ ስደተኞች መካከል ብዙዎቹ እስካሁን ያሉበት የሚታወቅ አይደለም፡፡

ምንም እንኳን የኤርትራ መንግስት ክሶቹን ቢያስተባብልም በርካታ ስደተኞች በኤርትራ መንግስት ታፍነው ተወስደዋል የሚሉ ክሶች ተደምጠዋል።

ከኤርትራ ድንበር ብዙም ሳይርቅ ተገንብተው የነበሩት የሽመልባ እና የህጻጽ ካምፖች ውስጥ ይገኙ የነበሩ የረድኤት ሰራተኞች ካምፖቹን ለቀው ሲወጡ ስደተኞቹ ለወራት ያህል ያለ ምግብ እና ሌሎች ወሳኝ አቅርቦቶች በከፍተና እንግልት ውስጥ ቆይተው ነበር።

የተወሰኑት ስደተኞች በትግራይ ክልል ደቡብ ምዕራባዊ ክፍል ወደሚገኙ እና በአንጻራዊነት ደህንነታቸው ወደተጠበቁ መጠለያ ካምፖች መሄድ ችለው ነበር።

በአጎራባች የአማራ ክልል አዲስ መጠለያ ክምፕ ለመገንባትም መሬት መመደቡን የመድ የስደተኞች ኤጀንሲው ተናግሯል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራዊያን ስደተኞች እንዳሉ የመንግስት መግለጫዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img