Monday, September 23, 2024
spot_img

የወይዘሮ አበበች ጎበና የቀብር ሥነ ሥርዐት በዛሬው እለት ይፈጸማል

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 29፣ 2013 ― የበርካታ ኢትዮጵያን ሕጻናት እናት የነበሩት የወይዘሮ አበበች ጎበና የቀብር ሥነ ሥርዐት በዛሬው እለት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም የመሠረቱት የበጎ አድራጎት ማኅበር አሳውቋል፡፡

በዚህ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በሚደረገው ሥነ ሥርዐት፣ በዛሬው እለት እስከ አምስት ሰአት ድረስ በአበበች ጎበና የሕፃናት ክብካቤና ልማት ማኅበር በሚደረግ ሽኝት የሚጀምር ነው፡፡

በተጨማሪም ከ5 እስከ 6 ስዓት ወደ መስቀል አደባባይ ሽኝቱ የሚቀጥል ሲሆን፣ ከ6 እስከ 8 ሰዓት ድረስ የሚቆይ ልዩ ልዩ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ፣ ከ8 ስዓት ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሽኝት ተደርጎ የቀብር ሥነ ስርዓታቸው በክብር እንደሚፈጸም ከወጣው መርሐ ግብር ተመልክተናል፡፡

የበጎ አድራት ማኅበራቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን የአበበች ጎበና አሸኛኘት እና የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኙ ጠይቋል፡፡

ወይዘሮ አበበች ጎበና በ85 ዓመታቸው ማረፋቸው የተነገረው እሑድ ሰኔ 27 ማለዳ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img