Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ስብሰባ ያደርጋል

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ሰኔ 27፣ 2013 ― የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ሰኞ ሰኔ 28፣ 2013 ከጠዋቱ 3 ሰአት ጀምሮ ስብብባ ያካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሚያካሂድ ሲሆን፤ የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቀው ይጠበቃል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በይፋዊ ገጽ ላይ አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img