Monday, September 23, 2024
spot_img

ዜና እረፍት

ወይዘሮ አበበች ጎበና ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ባለፉት 41 ዓመታት ብዙ መቶ ሺሕ ህፃናትን ተንከባከበው ለቁም ነገር ያበቁት ወይዘሮ አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የመሠረቱት የበጎ አድራጎት ማኅበር አሳውቋል፡፡

ወይዘሮ አበበች ጎበና ያለፉትን ሳምንታት በኮቪድ19 ቫይረስ ተይዘው በጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ ቢሆንም፣ ዛሬ ማለዳ ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል፡፡

በ1928 በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ በግራር ጃርሶ ወረዳ በቶርበን አሼ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሸበል አቦ በተባለች የገጠር መንደር የተወለዱት ወይዘሮ አበበቸ ጎበና፣ በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የቅርብ ወዳጆቻቸው እዳዬ በሚል ቁልምጫ የሚጠሯቸው አበበች ጎበና፣ ድህነትን በተለይም የህፃናት ጉስቁልናን መቅረፍ የሚቻለው ‹‹በግለሰብ ደረጃ ለምፅዋት በሚወረወሩ ሽርፍራፊ ሳንቲሞች ሳይሆን በአንድነት በማበር እና ያለንን አቅም በማሰባሰብ በችግር ላይ ያሉ ወገኖቻችንን በተለይም ሴቶችን ስናበቃ ነው›› በሚል እምነት ለብዙ ሕፃናት አለኝታ ሆነዋል፡፡

አምባ ዲጂታል የአገር ባለውለታ በሆኑት እናት ኅልፈት የተሰማውን ሐዘን ይገልጻል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img