Sunday, September 22, 2024
spot_img

የጸጥታው ምክር ቤት የሕወሃት ኃይሎች በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ አሳሰበ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሰኔ 26፣ 2013 ― የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት የሕወሃት ኃይሎች ‹‹በአስቸኳይ እና ሙሉ በሙሉ›› የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በትናንትናው እለት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ይፋዊ ስብሰባ ላይ ነው ይህ የተነገረው።

የመንግሥታቱ ድርጅት የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ በኤርትራ ሠራዊት እና በአማራ ክልል ኃይሎች በሚደገፈው የፌደራሉ መንግሥት ጦር እና በትግራይ መከላከያ ኃይል መካከል ተጨማሪ ግጭቶች ሊከሰት ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ሮዝመሪ ‹‹የበለጡ ግጭቶች ሊከሰቱ የሚችሉበት እና የፀጥታው ሁኔታው በፍጥነት ሊያሽቆለቁል የሚችልበት ሁኔታ አለ›› ካሉ በኋላ፤ ‹‹የትግራይ መከላከያ ኃይል የተኩስ አቁም ስምምነቱን በአፋጣኝ እና ሙሉ በሙሉ እንዲያጸድቅ›› መጠየቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመልክታል፡፡

የፌደራሉ መንግሥት መቀለን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የሕወሃት ኃይሎች ዳግም ሰኞ ሰኔ 21 የትግራይ ክልል መቀመጫ ከተማዋን መቆጣጠራቸው ይታወሳል።

የፌደራሉ መንግሥት መቀለን ለቅቆ ወጥቶ ግጭቱ እንዲቆም እና የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ በሚል ምክንያት ነበር።

ሆኖም በትላንተናው እለት መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን የፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ቢያደርግም፣ ህወሓት ግን አሁንም ግጭት እያስነሳ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተለይም በኮረም በኩል የትግራይ ልዩ ኃይል ተኩስ ከፍቶ እንደነበርም አንስተዋል።

ከቀናት በፊት የተናገሩት የሕወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ፣ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ‹‹ወደ አማራ ክልል መሄድ ካለብን እንሄዳለን፤ ወደ ኤርትራ መዝመት ካለብን እናደርገዋለን›› ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img