Sunday, October 13, 2024
spot_img

ሕወሃት በአገሪቱ ላይ የደኅንነት ሥጋት ሆኖ እንዳይቀጥል ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 25፣ 2013 ― የመከላከያ የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪው ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ከክፍሉ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሕወሃት ከሰሜን ዕዝ የዘረፋቸውን የአገር መጠበቂያ ትጥቆች ይዞ ለመዋጋት ቢሞክርም፣ ‹‹በሰራዊታችን ጀግንነትና አይበገሬነት በሶስት ሳምንት ውስጥ የመደበኛ ውጊያ መዋጋት እንዳይችል አድርጎ ደምስሶታል›› ብለዋል፡፡

በመደበኛ ውጊያ ተመቶ የተበታተነው ኃይል በሽምቅ ውግያ ለመዋጋት ቢሞክርም፣ ሰራዊቱ የሕወሃትን አመራሮችና ተዋጊዎቹን ከተደበቁበት ‹‹እየለቃቀመ በመደምሰስ እና ለህግ በማቅረብ የፈፀመው ግዳጅ›› የተሳካ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት የሕወሃት ቡድን በመደበኛም ይሁን በሽምቅ የመዋጋት አቅም እንዳይኖረው አድርጎ በመደምሰሱ፣ ሃይሉ አማራጭ ያደረገው የውሸት ፕሮፖጋንዳ በመስራት ህዝቡ ውስጥ ገብቶ ህፃናትንና አዛውንትን ከፊት አስቀድሞ መዋጋትን ነው ብለዋል፡፡

ሰራዊቱ በትግራይ ክልል ሕግን ለማስከበር 8 ወር ሲቆይ፣ ህዝቡ የሰላም ተጠቃሚ እንዲሆንና ሰብአዊ አገልግሎቶችና ድጋፎች ለህዝብ እንዲደርሱ መስዋዕትነትን በመክፈል ጭምር ያገለገለ ቢሆንም፣ ከህዝቡ የተሰጠው ምላሽ ግን በተቃራኒው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አክለውም የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላትና የጥሞና ግዜ ለመስጠት መንግስት በወሰነው ውሳኔ መሰረት፣ ሰራዊቱ መቀሌን ለቆ ሲወጣ ‹‹በሕዝብ መሃል ተደብቆ የነበረው ሃይል መሃል ከተማ ወጥቶ ጨፈረ እንጂ ከሰራዊታችን ጋር አልተዋጋም የመወጋትም አቅም የለውም›› ማለታቸውንም የመከላከያ ሠራዊት ገጽ አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img