Friday, November 29, 2024
spot_img

መንግሥት ‹‹ሰላም ፈላጊ›› የሕወሓት አባላትን ያካተተ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 25፣ 2013 ― መንግሥት የትግራይን ቀውስ ለመፍታት ሰላማዊ መንገድን የሚመርጡ የሕወሓት አባላትን ጨምሮ ሁሉንም ያካተተ ውይይት ለማድረግ መዘጋጀቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ይህንኑ የመንግሥት ሐሳብ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ከሚኒስቴር ዲኤታው አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን ጋር ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ በዚህ ጊዜ እንዳሉት፣ መንግስት በትግራይ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ሕጋዊ ከሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ሰላማዊ መንገድን ከመረጡ የሕወሓት አባላት፣ የግል ባለሀብቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ባለደርሻ አካላት ጋር አካታች ውይይት ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው ያስታወቁት፡፡

የፌደራል መንግስት በትግራይ የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራ ለጊዜው የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉንም ተናግረዋል።

መንግስት የተናጠል ተኩስ ቢያውጅም፣ የትግራይ ልዩ ኃይል በኮረም በኩል ተኩስ መክፈቱንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው መንግሥት ያወጀው የተናጠል ተኩስ አቁሙ እርምጃን ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ እንዳደነቀው ገልጸው የባንክ፣ የመብራትና የስልክ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ህወሓት እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል።

ባንኮች በሚመለከት ለትርፍ ስለሚሰሩ፤ ዋስትና ካልተገባላቸው ለመስራት እንደሚቸገሩ ያነሰት አምባሳደር ሬድዋን፤ መንግስት ግን ባንኮችን አስገድዶ ባንኮችን አገልገሎት ጀምሩ ማለት እንደማይችል አስረድተዋል ሲል የዘገበው አል ዓይን ሚዲያ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img